በአማራ ክልል ታላላቅ ከተሞች ላይ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ መርሃግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል ታላላቅ ከተሞች ላይ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ መርሃግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል
ባህርዳር፤ግንቦት 18/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሚገኙ ታላላቅ ከተሞች የብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ መካሄድ የጀመረውም በባህርዳር፣ በጎንደር፣ በደሴ፣ በኮምበልቻ፣ በደብረ ብርሃን፣በመተማና በሌሎች ዋና ዋና እንዲሁም መካከለኛ ከተሞች ነው።
በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች እየተሰሙ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በመገኘት መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ከፍተኛ የፌደራልና የክልል አመራሮችም በሚወዳደሩባቸው ከተሞች በመገኘት ለመራጩ ህዝብ መልእክት እንደሚያስተላልፉም ታውቋል።