ቀጥታ፡

በወላይታ ሶዶ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 18/2018(ኢዜአ)፡- በወላይታ ሶዶ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ወጣቶች፣ ሴቶችና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

ሰልፈኞቹ አሁን ላይ ወደ ወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም በማምራት ላይ ሲሆኑ፤ ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችንም እያስተላለፉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም