ቀጥታ፡

የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በደብረ ማርቆስና በደሴ ከተሞች እየተካሄደ ነው

በደብረ ማርቆስ/ደሴ፤ግንቦት 18/2018 (ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በደብረ ማርቆስና በደሴ ከተሞች እየተካሄደ ነው።

ከማለዳው ጀምሮ በደብረ ማርቆስ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ውጤታማ ተግባራት የተመለከቱ መልእክቶች እየተላለፉ ነው።

የድጋፉ ሰልፈኞች ከፓርቲው ጎን መቆማቸውን የሚያሳዩ መልዕክቶችን በማንገብ ድጋፋቸውን እየገለጹ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይም በደሴ ከተማና አካባቢዋ ብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

#ኢዜአ

#ምርጫ

#Ethiopian_News_Agency

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም