ቀጥታ፡

ብልጽግና ለቃሉ የታመነ በተግባር ተፈትኖም በድል የተወጣ ፓርቲ ነው - አቶ ሞገስ ባልቻ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 18/2018(ኢዜአ) ፦ ብልጽግና ፓርቲ ለቃሉ የታመነ በተግባር ተፈትኖም በድል ያጠናቀቀ መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።

የብልጽግና ፓርቲ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።

ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደው መርሀ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል አዳነች አቤቤ፣ ምክትል ከንቲባ እና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል ጃንጥራር አባይ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሞገስ ባልቻ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ቡዜና አልከድር፣ፓርቲውን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች እና የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎቾ ተገኝተዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ባለፉት አመታት በተከናወኑ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል።

አዲስ አበባን ከድንግዝግዝ እንቅልፍ በማውጣት ስሟን ከግብሯ ጋር ማገናኘት መቻሉንም ተናግረዋል።

በመደመር መንገድ በጠንካራ የስራ ባህል ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የ50 አመት ስራዎች በአምስት አመት ውስጥ ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ለቃሉ የታመነ በተግባር ተፈትኖም በድል ያጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል።

በመደመር መንገድ ተጉዘን ወዳሰብነው እንደርሳለን ያሉት ኃላፊው እየተከናወኑ ያሉ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ህብረተሰቡ ለብልጽግና ፓርቲ ድምጹን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም