ሠራዊቱ በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ እያከናወነ ያለው አርዓያነት ያለው ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
ሠራዊቱ በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ እያከናወነ ያለው አርዓያነት ያለው ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል
ድሬዳዋ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- የሀገር መከላከያ ሠራዊት በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ እያበረከተ ያለውን ሚና አጠናክሮ መቀጠሉን የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አስታወቀ።
ትምህርት ቤቱ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ያሰለጠናቸውን ወታደሮች ዛሬ እያስመረቀ ነው።
የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ኃላፊ ሻለቃ አክሊለ ለገሠ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ተመራቂዎቹ በተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሥር በሶማሊያ አውስኦም እና በአፍሪካ ሕብረት ስር በደቡብ ሱዳን ዩናሚስ ለሚሰማሩ ክፍሎች የቅድመ ስምሪት ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።
ሠራዊቱ የተጣለበትን የሀገር ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር የማስከበር ኃላፊነት በከፍተኛ የሙያ ብቃትና በማይናወጥ መስዋዕትነት እየተወጣ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ለዓለም ሰላም መከበርና መረጋገጥ እያበረከተ የሚገኘውን የላቀ አስተዋፅዖ እና የተጣለበትን ዓለም አቀፋዊ ኃላፊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ መቀጠሉን አረጋግጠዋል።
ተመራቂዎቹ ተልዕኳቸውን በላቀ ብቃት በመወጣት የኢትዮጵያ ሠራዊት በዓለም አደባባይ ያለውን ዝና እና ሕዝባዊ ተወዳጅነት ያስቀጥላሉ ብለዋል።