ቀጥታ፡

‎በጋራ ዕውቀትና ዓላማ፣ይበልጥ ጤናማ የሆነች አፍሪካን አብረን መገንባታችንን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፦‎በጋራ ዕውቀትና ዓላማ፣ይበልጥ ጤናማ የሆነች አፍሪካን አብረን መገንባታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፥ በኢትዮጵያ በልዩ የሕክምና ዘርፍ ሥልጠና ላይ ከሚገኙ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከመጡ 400 በላይ የሕክምና ባለሙያዎች መካከል፤ከሩዋንዳ ከመጡ 128 የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በጋራ ማዕድ ቆርሰናል ሲሉ ገልጸዋል።


 

እነዚህ ባለሙያዎች የአኅጉራችን የጤና ዘርፍ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚጠይቀውን ከፍተኛ ዕውቀትና የላቀ ብቃት ለማሟላት ታምነው እየተጉ ያሉ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።

ባለሙያዎቹ ቀጣዩን አፍሪካዊ ትውልድ በሕክምና ዘርፍ የሚኖረውን የመሪነት ሚና በማረጋገጥ ላይ የሚገኙ ተቋማት አካል ናቸው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በጋራ ዕውቀትና ዓላማ፣ ይበልጥ ጤናማ የሆነች አፍሪካን አብረን መገንባታችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም