ቀጥታ፡

ሀገር አቀፍ የአደባባይ የጸሎት መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ነው

አዲስ አበባ፤ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፦ሀገር አቀፍ የአደባባይ የሰላም እና አብሮነት የጸሎት መርሀ ግብር በመካሄድ ላይ ነው።




የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ  "ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን"  በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የአደባባይ የሰላም እና አብሮነት የጸሎት መርሀ ግብር በማካሄድ ላይ ነው።




በአራዳ ፓርክ እየተካሄደ ባለው መርሀ ግብር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች፣የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘው ተሻገር፣በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ፣የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣የተለያዩ ቤተ እምነቶች አባቶች፣አባ ገዳዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም