ቀጥታ፡

ባየር ሙኒክ የጀርመን ጥሎ ማለፍ ዋንጫን አነሳ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፦ በጀርመን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ (DFB-Pokal) ባየር ሙኒክ ስቱትጋርትን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በበርሊን በሚገኘው የኦሊምፒክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሃሪ ኬን ሁለት በጨዋታ እና አንድ በፍጹም ቅጣት ግቦች በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

ኬን በዘንድሮው የውድድር ዓመት ያስቆጠራቸውን አጠቃላይ ጎሎች 61 አድርሷል።

ባየር ሙኒክ በተጋጣሚው ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ባየር ሙኒክ ለ21ኛ ጊዜ የጥሎ ማለፉን ዋንጫ አንስቷል።

ሙኒክ ከጀርመን ቡንድስሊጋ እና የፍራንዝ ቤከንባወር የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በኋላ ሶስተኛ ዋንጫውን አንስቷል።

የባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ የነበረው ስቱትጋርት የዋንጫ ክብሩን ማስጠበቅ አልቻለም።

ቡድኑ የውድድሩ የአራት ጊዜ አሸናፊ ነው።

የጀርመን ጥሎ ማለፍ  91 ዓመታትን ያስቆጠረ ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም