ቀጥታ፡

ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ተገንብተው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል-አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር፤ ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ተገንብተው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።


 

በዚህ ወቅትም ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት፣ በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛሉ። 

በተለይም የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ መገንባት የክልሉን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የበለጠ በማሳደግ ረገድ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።


 

በዘመናዊ ትምህርት የታነፀና በእውቀት የበለፀገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማፍራት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ነው ያነሱት። 

በቀጣይም ፕሮጀክቶቹ በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም