ቀጥታ፡

በደቡብ ወሎ ዞን አርሶ አደሮች እያከናወኑት ያለው የግብርና ልማት ለምግብ ሉዓላዊነት እቅድ ተደማሪ አቅም የሚሆን ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ወሎ ዞን አርሶ አደሮች እያከናወኑት ያለው የግብርና ልማት ለምግብ ሉዓላዊነት እቅድ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ምክትል ጠቅላይ ሚስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፣ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች በግብርና ልማት አብዮት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የሃይቅ ዙሪያ አርሶ አደሮች መሬት እና እርሻቸውን ከጫት ወደ ሙዝ ክላስተር አሸጋግረው በአዲስ የልማት ግስጋሴ ላይ ናቸው ብለዋል።


 

አርሶ አደሮቹ የአካባቢን አንጻራዊ የልማት ጉልበት መለየት እና ወደ አትራፊ እና ዘላቂ የግብርና ጎዳና መሸጋገር ይገባል የሚለውን ሃገራዊ መርህ እና ስምሪት ተግብረው ማሳየተቻውን አመልክተዋል።

በዞኑ የለጋምቦ እና የመቅደላ ወረዳ አርሶ አደሮች በስንዴ ልማት አብዮት የእርሻ ከባቢያቸውን የስንዴ ስጋጃ እያለበሱ መሆናቸውን ነው ያብራሩት።

ይህ በዞኑ እየታየ ያለው የልማት ትጋት ኢትዮጵያ ለጀመረችው ለምግብ ሉዓላዊነት የጨከነ እቅድ እና ተግባር ተጨማሪ ጥሪትና ወረት እንደሆነም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም