ቀጥታ፡

ሸማችና አምራቹን በቀጥታ የሚያገናኙ የገበያ ማዕከላት

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ህብረተሰቡ ሸማች እና አምራቹን በቀጥታ ከሚያገናኙ የገበያ ማዕከላት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምት ጥሪ አቅርበዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ኑ በተመጣጣኝ ዋጋ ሸምቱ ሲሉ አስፍረዋል።


 

እነዚህ ማዕከላት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርት በማቅረብ የደላላን ሰንሰለት በመበጣጠስ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የተደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት ከጀመሩት ከእነዚሁ ሰባት የገበያ ማዕከላት በመገበያየት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም