ቀጥታ፡

በክልሉ የመንግስት ሰራተኛው ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ ይሰራል

ባህርዳር፤ ግንቦት 13/2018(ኢዜአ)፦ የመንግስት ሰራተኛው ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የድርሻውን መወጣቱን እንደሚቀጥል የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማርያም ገለጹ።

‎‎የመንግስት ሰራተኛውን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያወያይ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።


 

የቢሮ ኃላፊዋ በወቅቱ እንደገለፁት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉና ለሀገር እድገት ዘላቂ መሰረት የጣሉ የልማት ፕሮጀክቶች መተግበራቸውን ገልፀዋል።

በየደረጃው እየተመዘገበ ላለው ውጤት የመንግስት ሰራተኛው ፈጣንና ፍትሐዊ አገልግሎት በመስጠት የልማት ስራዎች በመደገፍ የድርሻውን መወጣቱን መቀጠል ይገባዋል ነው ያሉት።

ኮሪደርን መሰረት ያደረገው የከተሞች ልማት፣ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የበጋ ስንዴና ሌሎች ኢንሼቲቮች በክልሉ ውጤት ከተመዘገበባቸው መስኮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

‎በትምህርትና በጤናው ዘርፎችም ይታዩ የነበሩ ችግሮችን ለማቃለል በተከናወኑ ተግባራት ጤናማ፣ ብቁና ሀገር ወዳድ ዜጋ ማፍራት እየተቻለ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

የተጀመሩ የልማት ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል የመንግስት ሰራተኛው የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል ሲሉ አስገንዝበዋል።


 

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ስንታየሁ ስንሻው እና አቶ ላመስግን አዳነ እንደገለጹት፤ የክልሉን የሀገር ልማትና ዕድገት በማፋጠን የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።


 

በተለይም ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት ላይ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም