ቀጥታ፡

በክልሉ ባለፉት የለውጥ አመታት በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የታየው እመርታዊ ለውጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል 

ጋምቤላ ፤ ግንቦት 13/2018 (ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል  ባለፉት የለውጥ አመታት በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የታየው እመርታዊ ለውጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ገለፁ።

''የጋምቤላ ክልል የለውጥ ብርሀን'' በሚል መሪ ሃሳብ የክልሉ መንግስት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ዛሬ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው። 


 

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ባለፉት የለውጥ አመታት መንግስት ለዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ሴክተር ትኩረት ሰጥቶ ባከናወናቸው ተግባራት በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። 

በዚህም ክልሉ ያሉትን እምቅ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማልማት የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። 

በቀጣይም ለኢኮኖሚ ዘርፉ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ  በመጠቀም የክልሉን የተፈጥሮ ሃብት ይበልጥ በማልማት እንደ ክልልም ሆነ እንደ ሀገር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን  በትጋት ይሰራል ብለዋል። 

በተለይም የግብርና ምርቶችን  በማቀነባበር ለሚሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ማበረታቻ ማቅረብ ላይ  በትኩረት እንደሚሰራም አመልክተዋል። 

የከተሞችን እድገት ለማፋጠን መሰረት የሚጥሉ ተግባራትን እንደ ኮሪደር ልማትና የመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎትን በማስፋት የመንግስትን አገልግሎት የማቀላጠፍ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። 

በቀጣይም  የክልሉን የልማት እቅዶች በበለጠ ለማሳካት ቅንጅታዊ  ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ ምሁራንና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም