ቀጥታ፡

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል መሪ ሐሳብ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018 (ኢዜአ)፦ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት በሚል መሪ ሐሳብ የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ መድረክ በምርታማነት ጉዳይ ቁጭት ፈጥሮ የሚተጋ ማህበረሰብ መገንባትን ያለመ ነው።

ከዚህ ቀደም በአዳማ እና በሃዋሳ በተዘጋጁ ተመሳሳይ መድረኮች የየክልሉን ተሞክሮ የዳሰሱ ውይይቶች ተካሂደዋል።

የተለያዩ ክልሎችም ከተረጅነት ወደ ምርታማነትና ወደ ሉዓላዊ ክብር ለመጓዝ እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራት ተዳሰዋል።


 

በዛሬው መድረክ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ሮዛ ዑመር፣ በድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ኢብራሂም ዩሱፍ ተገኝተዋል።

እንዲሁም የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር፣ ከሶማሌ፣ ከሐረሪ እና ከአፋር ክልሎች የተውጣጡ አርሶ አደሮች በመድረኩ እየተሳፉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም