ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ቡና ወደ ድል ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር አዳሙ (በፍጹም ቅጣት ምት) እና ሀብታሙ አሸናፊ ለቡናማዎቹ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ኪሩቤል ዳኜ የፋሲል ከነማን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና በ46 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም 12ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ 46 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ከነበረበት አራተኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም