በወራጅ ቀጠና የሚገኘው መቀሌ 70 እንደርታ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል - ኢዜአ አማርኛ
በወራጅ ቀጠና የሚገኘው መቀሌ 70 እንደርታ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ ሸገር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቦና ዓሊ በ91ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ከአራት የሊጉ ጨዋታዎች ወደ አሸናፊነት የተመለሰው መቀሌ 70 እንደርታ በ34 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቀሌ 70 እንደርታ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በሚያደርገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በሊጉ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ በ40 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በውድድር ዓመቱም ዘጠነኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።