ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙኀን ሚና ላይ የሚመክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙኀን ሚና ላይ የሚመክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ “ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙኀን ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ አዘጋጅተውታል።
በመድረኩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የስራ ሃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን የስራ ሀላፊዎች እና ጋዜጠኞች ታድመዋል።
መድረኩ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ለማስገንዘብ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በዚህ ሂደት ውስጥ የመገናኛ ብዙኀን እና የሲቪል ማህበራት ሚና እጅግ ወሳኝ መሆኑም ተጠቅሷል።