ቀጥታ፡

የመውረድ ስጋት ያለበት ቶተንሃም ሆትስፐርስ በቼልሲ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት ቼልሲ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኤንዞ ፈርናንዴዝ እና አንድሬ ሳንቶስ የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።

ሪቻርልሰን ለቶተንሃም ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።




በውድድር ዓመቱ 17ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቶተንሃም በ38 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቢሸነፍም በ38ኛ ሳምንት ከኤቨርተን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ አንድ ነጥብ ካገኘ በሊጉ መቆየቱን ያረጋግጣል።

ከሰባት የሊግ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቼልሲ በ52 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም 14ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም