ቀጥታ፡

አርሰናል ከ22 ዓመት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቦርንማውዝ እና ማንችስተር ሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ትናንት ማምሻውን በቫይታሊቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጁኒየር ክሩፒ በ38ኛው ደቂቃ የቦርንማውዝን ጎል አስቆጥሯል።

አርሊንግ ሃላንድ በ95ኛው ደቂቃ ሲቲን አቻ አድርጓል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ እና አዝናኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ማንችስተር ሲቲ አቻ መውጣቱን ተከትሎ አርሰናል በ82 ነጥብ አንድ ጨዋታ እየቀረው ከ22 ዓመት በኋላ የሊጉ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።




የአርሰናል የ22 ዓመት የሊጉ የዋንጫ ጥበቃትናንት ማምሻውን አብቅቷል።

በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ በ78 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

በውድድር ዓመቱ 14ኛ ድሉን ያስመዘገበው ቦርንማውዝ በ56 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ቦርንማውዝ ባለፉት 17 የሊግ ጨዋታዎች ባለመሸነፍ ድንቅ ግስጋሴ ላይ ይገኛል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በ38ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም