መቻል የሊጉ መሪ መሆን የሚችልበትን እድል ሳይጠቀምበት ቀረ - ኢዜአ አማርኛ
መቻል የሊጉ መሪ መሆን የሚችልበትን እድል ሳይጠቀምበት ቀረ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና መቻል አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንተነህ ተፈራ በአራተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ባህር ዳር ከተማን መሪ አድርጓል።
ፈቱዲን ጀማል በ82ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል መቻልን አቻ አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ53 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት መረከብ የሚችልበትን እድል አልተቀመበትም።
ባህር ዳር ከተማ በ45 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ዘንድሮው በርካታ የአቻ ውጤት (18) ያስመዘገበ ቡድን ነው።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ከሁለት ተከታታይ የሊግ ድሎች በኋላ አቻ የወጣው ሀዲያ ሆሳዕና በ42 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሳሳይ 42 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የ33ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ወላይታ ድቻ ያለ ግብ አቻ በመውጣት ነጥብ ተጋርተዋል።