ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ድልድል ዛሬ በግብጽ ካይሮ ወጥቷል።
ኢትዮጵያ በምድብ 10 ከሴኔጋል፣ ሞዛምቢክ እና ሱዳን ጋር ተደልድላለች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቅድመ ማጣሪያ ሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔን በድምር ውጤት 4 ለ 0 በማሸነፍ ለምድብ ድልድሉ መብቃቱ የሚታወስ ነው።
በድልድሉ መሰረት 48 ሀገራት በ12 ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የምድብ ጨዋታዎች በመስከረም፣ ህዳር እና መጋቢት 2019 ዓ.ም ባሉ ዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድኖች መርሐ ግብር ወቅት ይካሄዳሉ።
ከ48ቱ ሀገራት መካከል 21ዱ ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፉሉ።
አዘጋጆቹ ኬንያ፣ ታንዛንያ እና ዩጋንዳ በቀጥታ በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ።
እ.አ.አ በ2027 በሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ።