ቀጥታ፡

በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ የመጠጥና የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ 

ሰመራ ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ የመጠጥና የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

ፕሮጀክቶቹን መርቀው ስራ ያስጀመሩት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ናቸው።

የተመረቁት ፕሮጀክቶች ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ይገጥማቸው የነበረውን የመጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት የሚፈቱ መሆኑ ተመላክቷል።


 

በተለይም  አርብቶ አደሮች ውሃ ለማግኘት ሩቅ አካባቢዎች በመሄድ ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት የሚያስቀር መሆኑም ታውቋል።

የመስኖ ፕሮጀክቱም የክልሉ አርብቶና አርሶ አደሮች በአካባቢው ያለውን ሰፊ መሬት በማልማት ምርታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም