ቀጥታ፡

አርሰናል የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይበልጥ የተቃረበበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል በርንሌይን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ካይ ሃቫርትዝ በ36ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎል አስቆጥሯል።

አርሰናል በሊጉ ከማዕዘን ምት ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት 24 አድርሷል።

ባለሜዳው አርሰናል የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ 25ኛ ድሉን ያስመዘገበው የሊጉ መሪ አርሰናል በ82 ነጥብ ወደ ዋንጫው ይበልጥ የቀረበበትን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።

ተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ነገ ከቦርንማውዝ ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ከጣለ አርሰናል የሊጉ አሸናፊ መሆኑን ያረጋግጣል።

በአንጻሩ በሊጉ 24ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው በርንሌይ በ21 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዟል።

በርንሌይ ከሊጉ መውረዱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም