ቀጥታ፡

ፓርቲው የሴቶችን እና ወጣቶችን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክሮ እየሰራ ነው

ሰቆጣ ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች የልማት ስራዎች የሴቶችን እና ወጣቶችን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክሮ መስራቱ ተመላከተ። 

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ ሴቶችና ወጣቶችን ያሳተፈ የብልፅግና ፓርቲ የዕጩዎች ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄዷል።


 

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንታይቱ ካሴ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ብልፅግና ፓርቲ በሚካሄዱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች የልማት ስራዎች  የሴቶችን እና ወጣቶችን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክሮ ሰርቷል።

በዚህም የሴቶችና የወጣቶችን የመሪነት ሚና በማሳደግ፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በትምህርትና በጤና የልማት ስራዎች በማሳተፍ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዳግም ባይነሳኝ በበኩላቸው፤  ፓርቲው ተምሳሌት የሆነችን ሃገር ለመገንባት በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።


 

ሴቶችና ወጣቶቹ ምርጫው ሰላማዊ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እስካሁን እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል።

በሰቆጣ ከተማ በተካሄደው የሴቶችና የወጣቶች መድረክ ላይ አመራሩ፣ የወጣትና የሴቶች አደረጃጀቶች ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም