ቀጥታ፡

መረጃ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት እና የመረጃና የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ነው 

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦መረጃ ልክ እንደ ወርቅ ውድ የሀገር ሀብት ከመሆኑም ባለፈ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት እንዲሁም የመረጃና የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።


 

በንግግራቸው እንዳነሱት፣ መረጃ ልክ እንደ ወርቅ ውድ የሀገር ሀብት ከመሆኑም ባለፈ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት እንዲሁም የመረጃና የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከሌሎች በሚገኝ መረጃ ላይ ሙሉ ለሙሉ መደገፍ የፖሊሲ ነጻነትን የሚያሳጣና ትክክለኛነቱ የሚያጠራጥር በመሆኑ፣ የራስን መረጃ በሀገር ልጅ መሰብሰብና መተንተን ትልቅ ሀገራዊ ኩራትና ዋስትና መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም የዳታ ምንጮችን በማብዛትና እርስ በርስ በማነፃፀር የጠራና የዘመነ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋት ለሀገር እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

በተጨማሪም ይህንን ጥራትና ተደራሽነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) ቴክኖሎጂን በግልና በመንግስት ተቋማት ውስጥ በጥልቀት መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም