በቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ፎረም በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ፎረም በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው ሰላም እና ደህንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ፎረም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ፎረሙ የሚካሄደው “ቀጣናዊ ተቋማትን ማጠናከር ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ” በሚል ሀሳብ ነው።
በፎረሙ መክፈቻ ላይ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከፍተኛ አመራሮች እና የማህበረሰብ መሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ቀጣናዊ መፍትሄዎች ለቀጣናዊ ችግሮች የሚል እሳቤን ማስተዋወቅ ዋና አላማው ያደረገው ፎረሙ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ በሰላም እና ፖለቲካዊ ምክክር ማእከል (CRPP)፣ በሶማሌ ክልል መንግስት እና በሌሎች አጋሮች በጋራ የተዘጋጀ ነው።
ቀጣናዊ ፎረሙ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።