ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ አርሰናል ከበርንሌይ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት አርሰናል ከበርንሌይ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የሁለቱ ክለቦች መርሐ ግብር ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል።

አርሰናል በ79 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ካሸነፈ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ ያደርጋል።

ጨዋታው ለመድፈኞቹ ዋንጫውን ለማንሳት እያደረጉት ባለው ጉዞ እጅጉን ወሳኝ የሚባል ነው።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ የዋንጫውን ዕድል ራሱ የመወሰን ዕድል አለው።

ከሊጉ መውረዱ የተረጋገጠው በርንሌይ በ21 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዟል።

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ አርሰናል 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

የ45 ዓመቱ ፖል ቲርኒ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም