በክልሉ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፡- በሀረሪ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ተጨባጭ ስኬቶች መመዝገባቸውን የክልሉ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ገለጸ።
የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ረምዚያ አብዱልወሃብ ባለፉት አምስት ዓመታት በሴቶች፣ሕጻናትና ወጣቶች ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶች በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በክልሉ ባለፉት አመታት የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በእነኚህ አመታትም 26 ሺህ 241 ወጣቶችና ሴቶችን በተለያዩ ተቋማት ብሎም ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል።
ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጋር ተያይዞ በክረምት በጎ ፈቃድ 46ሺህ 200 ወጣቶችን በማሳተፍ 216ሺህ 156 የህብረተሰብ ክፍሎችን በበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል።
ከተከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ውስጥም የአረጋውያንንና የአቅመ ደካማ ዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል።
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱም 402 ሚሊዮን 802 ሺህ 904 ሚሊዮን ብር የሚገመት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል።
በዚህም የ398 የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት በመገንባትና በማደስ ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካማ ዜጎች ማስረከብ ተችሏል ብለዋል።
ሴቶች በክልሉ ቁልፍ ተቋማትን በብቃት እየመሩ እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊዋ ይህም ሴቶች ለተሳትፎ ብቻ ሳይሆን በተግባር ውጤታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ አስችሏል ነው ያሉት።
ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችንና ወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎን ከማሳደግ አኳያ በተሰሩ ሰፋፊ ስራዎች ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በቀጣይም በሴቶች ፣ህፃናትና ወጣቶች ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች ለማስቀጠል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።