የምርጫው ሂደት ፖሊሲና ፕሮግራሞችን በነጻነት ለማስተዋወቅ እድል ፈጥሯል - ኢዜአ አማርኛ
የምርጫው ሂደት ፖሊሲና ፕሮግራሞችን በነጻነት ለማስተዋወቅ እድል ፈጥሯል
ሰቆጣ ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ፓርቲዎች ፖሊሲና ፕሮግራሞቻቸውን በነጻነት ለማስተዋወቅ እድል የፈጠረ መሆኑ ተመለከተ።
ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ፓርቲ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ ለሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ማኑፌስቶውንና እጩዎችን አስተዋውቋል።
የጥምረቱ የምርጫና ፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊና የአገው ብሄራዊ ሸንጎ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ አላምረው ይርዳው እንደገለጹት፤ ጥምረቱ የብሄር ብሄረሰቦች ስብስብ በመሆኑ ለእኩልነት መከበር ይሰራል።
ፓርቲው የብሄራዊ ጥቅም መከበርን ዋነኛ አላማው በማድረግ ለሰላምና ብሄራዊ መግባባት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ መልኩ በነጻነት በመንቀሳቀስ የፓርቲያቸውን ፖሊሲና ፕሮግራም ለማስተዋወቅ እድል የፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል።
በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ የፓርቲው አባላት በበኩላቸው ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል።