ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ መካከል ተከናውኗል።

በዚህም መሠረት፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእሙሽ ዳንኤል እና ረድዔት አስረሳኸኝ ግቦች ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎም፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት በአጠቃላይ ለ9ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል።

ቀደም ብሎ በተከናወነ የዕለቱ መርሐ-ግብር መቻል እና አዲስ አበባ ከተማ 2 አቻ ተለያይተዋል።

ይህን ተከትሎም መቻል በ56 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን ሲያጠናቅቅ፤ በ16 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አዲስ አበባ ከተማ ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ወርዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም