ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፡- በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኖቲንግሃም ፎረስትን በኦልድትራፎድ ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ 3 ለ 2 ረትቷል።

የማንችስተር ዩናይትድን ግቦች፤ በ5ኛው ደቂቃ ሉክ ሾው፣ ማቲውስ ኩንያ በ54ኛው ደቂቃ እንዲሁም ምቤሞ በ75ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የኖቲንግሃም ፎረስትን ግቦች ደግሞ፤ በ52ኛው ደቂቃ ሞራቶ በ77ኛው ደቂቃ ጊብስ ዋይት አስቆጥረዋል።

የጨዋታውን ውጤት ተከትሎም ማንችስተር ዩናይትድ በ68 ነጥብ ባለበት 3ኛ ደረጃ ላይ ሲሆን፤ ኖቲንግሃም ፎረስት በ43 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዓመቱ 20 ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል፤ በቴሪ ሄንሪ እና ኬቨን ዴብሮይን ተይዞ የነበረውን በአንድ ዓመት ብዙ ጎል አመቻችቶ የማቀበል ክብረ ወሰን ተጋርቷል።

የዕለቱ የጨዋታ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ፤ በተመሳሳይ 11 ሠዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከፓላስ፣ ሊድስ ከብራይተን፣ ዎልቭስ ከፉልሃም፣ ኤቨርተን ከሰንደርላንድ የሚጫወቱ ይሆናል።

በሌላ በኩል ኒውካስትል ከዌስትሃም ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ እንደሚጫወቱ የወጣው መርሐ-ግብር ያስረዳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም