በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና አዲስ አበባ ከተማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና አዲስ አበባ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መቻል እና አዲስ አበባ ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ትንቢት ሳሙኤል በጨዋታ እና ትዕግስት ወርቁ በፍጹም ቅጣት ምት ለመቻል ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ዓለምነሽ ገረመው ለአዲስ አበባ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ሁለት ግቦች ያስቆጠረችው ዓለምነሽ ገረመው የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
መቻል በ56 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን አጠናቋል።
ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የወረደው አዲስ አበባ ከተማ በ16 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋንጫውን ለማንሳት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።