ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ድሬዳዋ ገብተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ድሬዳዋ ገብተዋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ድሬዳዋ ገብተዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ የኢትዮጵያ መልክ፤ የፍቅር ርዕስ፣ የሥልጣኔና የዘመናዊነት ተምሳሌት ወደሆነችው ድሬዳዋ ገብተናል ብለዋል።
የምድር ባቡር ፈርጥ፣ የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል በሆነችው ድሬዳዋ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸው ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለከተማው ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በድሬዳዋ በሚኖራቸው ቆይታ በከተማዋ እየተሰሩ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙም ገልጸዋል።