ቀጥታ፡

በምግብ ራስን መቻል ዋነኛ አጀንዳችን ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፡- በምግብ ራስን መቻል ዋነኛ አጀንዳችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዛሬ ማለዳ ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በጎዴ እየተገነባ የሚገኘውን የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት ማብራሪያ፤ በምግብ ራስን ለመቻል መሬት ያስፈልጋል፣ ውኃ ያስፈልጋል፣ ሰው ያስፈልጋል እነዚህ ደግም አሉን ብለዋል።


 

ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ላይ እየሠራን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህን ካሟላን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የሚተርፍ ነገር ማድረግ ይቻላል ብለዋል።

ሶማሌ ክልል ለልማት በጣም የተመቸ አካባቢ መሆኑን ጠቁመው፤ ያለውን መሬትና ውኃ ወደ መስኖ በማስገባት በሶማሌ ብቻ የሚለማው ለብዙ እንደሚተርፍ አመላክተዋል።

ይህን ለማድረግም ሥራ፣ ሀብት እና ጊዜ እንደሚፈልግ አስረድተው፤ እነዚህን ካሳካን ብዙ ችግሮቻችንን የሚፈታ ጉዳይ ይሆናል ሲሉ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም