ቀጥታ፡

የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጨረሻ ቀን ውሎ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦  በጋና አክራ እየተካሄደ የሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል። 

ሻምፒዮናው ከግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጋና ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሲካሄድ ቆይቷል። 

በውድድሩ መዝጊያ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ። 

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው አምስት የወርቅ፣ አንድ የብር እና አምስት የነሐስ በድምሩ 11 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በሻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያ 31 ሴቶች እና 32 ወንዶች በድምሩ 63 አትሌቶችን አሳትፋለች። 

በውድድሩ ላይ ከ54 ሀገራት የተወጣጡ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም