ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት ዛሬ ስድስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ያስተናግዳል።

የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ያረጋገጠው ማንችስተር ዩናይትድ በ65 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ኖቲንግሃም ፎረስት በ43 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዩናይትድ ካሸነፈ በሊጉ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ያረጋግጣል።

ጨዋታው ጊዜያዊው አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በክለቡ በቋሚነት የሚቀጥልበት የሁለት ዓመት ውል በተፈራረመ ማግስት የሚደረግ መሆኑ ትኩረትን ስቧል።

በፕሪሚየር ሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው ኖቲንግሃም ፎረስት ከ36ኛ ሳምንት የአቻ ውጤት በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።
 


 

በሌላኛው መርሐ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከዌስትሃም ዩናይትድ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኒውካስትል ዩናይትድ በ46 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ዌስትሃም ዩናይትድ በ36 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የመውረድ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ዌስትሃም ዩናይት ካሸነፈ በጊዜያዊነት ከወራጅነት ቀጠና በመውጣት ቶተንሃም ሆትስፐርስ ላይ ጫና ያሳድራል።

በ36ኛ ሳምንት ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር አንድ አቻ የተለያየው ኒውካስትል ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል።




ብሬንትፎርድ ከክሪስታል ፓላስ፣ ሊድስ ዩናይትድ ከብራይተን፣ ዎልቭስ ከፉልሃም እና ኤቨርተን ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም