ማንችስተር ሲቲ ለስምንተኛ ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ለስምንተኛ ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኤፍኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶዋን ሴሜኒዮ በ71ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሴሜኒዮ የግል ድንቅ ብቃቱን ተጠቅሙ በተለምዶ ‘ቄንጠኛ’ በሚባል መልኩ ያስቆጠራት ጎል አስደማሚ የሚባል ነው።
ማንችስተር ሲቲ በተጋጣሚው ላይ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል። ድሉን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ የኤፍኤ ካፑን ዋንጫ ለስምንት ጊዜ አንስቷል።
ውሃ ሰማያዊዎቹ ከሶስት ዓመታት በኋላ አንጋፋውን ውድድር አሸንፈዋል። ሲቲ ከካራባኦ ካፕ በኋላ በዘንድሮው የውድደር ዓመት ሁለተኛ ዋንጫውን አገኝቷል።
በአንጻሩ ቼልሲ ለዘጠነኛ ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን የማንሳት ህልሙ አልተሳካም። ሰማያዊዎቹ ለመጨረሻ ጊዜ ውድድሩን ያሸነፈው እ.አ.አ 2018 ነው።
ቼልሲ ዋንጫውን ቢያነሳ ዩሮፓ ሊግ የመግባት እድል ያገኝ ነበር።