ወልዋሎ አዲግራት ዩኒርሲቲ ድል ሲቀናው ሃዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ አቻ ተለያይተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒርሲቲ ድል ሲቀናው ሃዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ አቻ ተለያይተዋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መካሄዱን ቀጥሏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ጋናዊው ኮንኮኒ ሃፊዝ እና እንዳልካቸው ጥበቡ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አቤል ሀብታሙ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ39 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 15ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ዘጠነኛ ድሉን አሳክቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ45 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው መርሐ ግብር ሃዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ሃዋሳ ከተማ በ45 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ባለፉት ዘጠኝ የሊጉ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ሃዋሳ ከተማ በውጤት ማጣት ቀውስ ይገኛል።
አርባምንጭ ከተማ በ29 ነጥብ የመጨረሻው 20ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም።