ይርጋጨፌ ቡና በሊጉ መቆየቱን ሲያረጋግጥ አዲስ አበባ ከተማ ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ወርዷል - ኢዜአ አማርኛ
ይርጋጨፌ ቡና በሊጉ መቆየቱን ሲያረጋግጥ አዲስ አበባ ከተማ ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ወርዷል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ሸገር ከተማ እና ይርጋጨፌ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄዷል።
የይርጋጨፌ ቡናዋ ግብ ጠባቂ የኔነሽ አበበ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ይርጋጨፌ ቡና በ19 12ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።
በአንጻሩ በ15 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ወርዷል።
አርባምንጭ ከተማ አስቀድሞ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ይታወቃል።
ሸገር ከተማ በበኩሉ በ48 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ የውድድር ዓመቱን አጠናቋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።