በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዝናሽ ሰለሞን እና ፊርማዬ ከበደ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አህላም ሲራጅ የአዳማ ከተማን ብቸኛ ጎል አስቆጥራለች።
የድሬዳዋ ከተማዋ አምበል ሊና መሐመድ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው ድሬዳዋ ከተማ በ28 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን አጠናቋል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 14ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በበኩሉ በ22 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።