ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊጉ የ25ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን መርሐ ግብር

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች ከድል የራቀው አዳማ ከተማ በ22 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ድሬዳዋ ከተማ በ25 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት አራት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።  ሁለቱም ቡድኖች ዓመቱን አሸናፊነት ለማጠናቀቅ ይጫወታሉ።

በሌላኛው መርሐ ግብር ሸገር ከተማ ከይርጋጨፌ ቡና ከረፋዱ አምስት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሸገር ከተማ በ47 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ይርጋጨፌ ቡና በ18 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በ26ኛ ሳምንት በቦሌ ክፍለ ከተማ 2 ለ 0 የተሸነፈው ሸገር ከተማ ዓመቱን በድል ለመቋጨት ይፋለማል።

ይርጋጨፌ ቡና ካሸነፈ ወይም አቻ ከወጣ በሊጉ መቆየቱን ያረጋግጣል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም