አስቶንቪላ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማለፉን አረጋገጠ - ኢዜአ አማርኛ
አስቶንቪላ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማለፉን አረጋገጠ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር አስቶንቪላ ሊቨርፑልን 4 ለ 2 ረቷል።
በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦሊ ዋትኪንስ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሞርጋን ሮጀርስ እና ጆን ማጊን ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ቨርጅል ቫን ዳይክ ለሊቨርፑል ጎሎቹን አስቆጥሯል።
በሊቨርፑሉ አማካይ ዶምኒክ ስቦዝላይ በተሰራው ስህተት ኦሊ ዋትኪንስ ያስቆጠረው ጎል የጨዋታው ቁልፍ ክስተት ነበር።
ሊቨርፑል በጨዋታው የሰራቸው ስህተቶች ዋጋ አስከፍሎታል።
ጨዋታው አዝናኝ እንቅስቃሴ የተደረገበት ሲሆን አስቶንቪላ ግልጽ የግብ እድሎችን በተሻለ ሁኔታ ፈጥሯል።
በሊጉ 18ኛ ድሉን ያስመዘገበው አስቶንቪላ በ62 ነጥብ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አንድ ጨዋታ እየቀረው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋግጧል።
በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊቨርፑል በ59 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመሳተፍ በ38ኛ ሳምንት ብሬንትፎርድን ማሸነፍ ይጠበቅበታል።