ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጨማሪ ሜዳሊያ አገኘች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጨማሪ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በጋና አክራ መካሄዱን ቀጥሏል።
ማምሻውን በተካሄደው የ10000 ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት አሰፉ አብርሃ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው ሶስት የወርቅ፣ አንድ የብር እና አራት የነሐስ በድምሩ ስምንት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
ሻምፒዮናው እስከ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።