ቀጥታ፡

ሃዋሳ ከተማ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሃዋሳ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ታደለች አብርሃም በ53ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥራለች።

የሃዋሳ ከተማዋ ትዕግስት አበራ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

በሊጉ 15ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ52 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን አጠናቋል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ43 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።

ዛሬ አስቀድሞ በተደረጉ የ25ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 0፣ ባህር ዳር ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም