በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኤልሳ ብርሃኑ፣ ምርጥነሽ ዮሐንስ እና ምትኬ ብርሃኑ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የሲዳማ ቡናዋ ምትኬ ብርሃኑ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጣለች።
በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና በ38 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የወረደው አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።
በውድድር ዓመቱ 20ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በሊጉ ያሸነፋው ጨዋታዎች ብዛት ሁለት ብቻ ናቸው።
ይህም አርባምንጭ ከተማን በሊጉ አነስተኛ ድል ያስመዘገበ ቡድን አድርጎታል።