መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ መድን ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ መድን ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ መድን አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጋናዊው አብዱል ጋንዩ በ67ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል መድን መሪ ሆኗል።
ብርሃኑ አዳሙ በ84ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ግብ ለመቀሌ 70 እንደርታ ወሳኝ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
መቀሌ 70 እንደርታ በ31 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ከሶስት ተከታታይ ድሎች በኋላ አቻ የወጣው ኢትዮጵያ መድን በ41 ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል።