ቀጥታ፡

ባህር ዳር ከተማ የውድድር ዓመቱን በድል ቋጭቷል


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አስቴር ደግአረገ እና ወርቅነሽ መሰለ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ረድኤት ዳንኤል ለልደታ ክፍለ ከተማ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

የባህር ዳር ከተማዋ ወርቅነሽ መሰለ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው ባህር ዳር ከተማ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። ዓመቱንም በድል አጠናቋል።

በውድድር ዓመቱ 16ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በተመሳሳይ 22 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም