የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ መርሐ ግብር የሚደረግባቸው ቀናቶች ይፋ ሆኑ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ መርሐ ግብር የሚደረግባቸው ቀናቶች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ድልድል ትናንት መውጣቱ ይታወቃል።
በእጣው መሰረት ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታዎቹ የሚደረግባቸውን ቀናት እና የመጫወቻ ሜዳ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ 70 እንደርታ ግንቦት 17፣ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን ግንቦት 18 በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።