በቅርቡ በህይወት ለተለዩት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለነበሩት ለአቶ ዘገየ አስፋው የሕሊና ጸሎት ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በቅርቡ በህይወት ለተለዩት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለነበሩት ለአቶ ዘገየ አስፋው የሕሊና ጸሎት ተደረገ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦በቅርቡ በህይወት ለተለዩት እና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለነበሩት ለአቶ ዘገየ አስፋው የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት ተደረገ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸው ተግባራት እና ቀጣይ አቅጣጫ እየተገመገመ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይም በቅርቡ በህይወት የተለዩት እና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ዘገየ አስፋው በአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት መታሰባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።