ቀጥታ፡

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው ውድድሮች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ በጋና አክራ እየተካሄደ የሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።

ምሽት 2 ሰዓት ከ05 ላይ የ10000 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል።

በውድድሩ ላይ አሰፉ አብርሃ፣ ስምረት በርሄ እና ዘይን አየልኝ ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ።

አትሌት ዘይን አየልኝ በ5000 ሴቶች የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል።

አትሌት ጌታሁን ታደሰ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ በሚካሄደው የወንዶች የ110 ሜትር መሰናክል የማጣሪያ ውድድር ላይ ይሳተፋል።

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው ሶስት የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሶስት የነሐስ በድምሩ ሰባት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ከነገ በስቲያ ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም